የተጠናከረ እውቀታዊ የሸሪዓ ፕሮግራም ሲሆን ጊዜ ገደቡ አንድ አመት ብቻ ነው። ስርዓተ-ትምህርቱ በአመት አንዴ ምዝገባው የሚከፍት ሲሆን እሱም ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት በቂ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ እና በአፍሪካ ቲቪ ላይ ይፋ ይደረጋል። የዲፕሎማው ፕሮግራም በውስጡ ሁለት ሴሚስተር የያዘ ሲሆን ተማሪዎቹ በነዚህ ሁለት ሴሚስተሮች በየአንዳንዱ ሴሚስተር ውስጥ ስድስት የትምህርት አይነቶችን ይማራል። ተማሪው የሁለቱም ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ካለፈ በኋላ ከአካዳሚው የማጠናቀቂያ ምስክር ወረቀት ይወስዳል።