የአፍሪካ አካዳሚ የ ሸሪአ ትምህርትን ያስተምራል ፣ በተለይ ለመርሃግብሩ የተዘጋጁትን ስድስት ኮርሶች እንደሚከተለው ያስተምራል-
በ አቂዳ የትምህርት ኮርስ ተማሪው ስለ አቂዳ ትርጉም አሕሉ ሱና ወልጀማዓ አቂዳ ላይ ስላላቸው አቋም ቀለል ባለ አቀራረብ እንዲሁም ከ ግጭት በራቀ መልኩ የ አቂዳ ትምህርትን ከምንጩ እና የ እስላማዊ አቂዳ ልዩ የሚያደርገውን ባህሪያት ተውሂድና የተውሂድ ክፍሎች በተውሂድ ላይ ስለተነሱ ብዥታዎች የተውሂደል ኡሉሂያ መሰረት ከ ኢአማኒያን እና መሰሎቻቸው ለሚነሱ ውዥንብሮች መልስ መጠት እንዲችሉ ተማሪዎችን በትምህርት ማነጽ ተክፊር ትርጉሙ እና ማእቀፉ የቂያማ ምልክቶች ስለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)ቤተሰቦች እና ባልደረባዎች ወሊዮች እና ከራማቸው ሸፋአ (ምልጃ) እና ሌሎችም
በተፍሲር የትምህርት ጊዜ ለተማሪዎች የሚቀርበው ስለ ተፍሲር መግቢያ የ ፋቲሃ ምእራፍ ትርጉም የ አያተል ኩርሲ ትርጉም የ በቀራ ምእራፍ መጨረሻ ትርጉም የ አማ ጁዝእ ትርጉም ከተሟላ ማብራሪያ ጋር ትምህርቱም ከ ቀደምትና ከቅርብ ጊዚያት የተፍሲር መጽሀፎች ተውጣጥቶ የተዘጋጀ ነው
በሀዲስ የትምህርት ወቅት ለተማሪዎች የሚቀርበው
አስፈላጊና ብዝሀ ትርጉም ያላቸውን የተመረጡ ሃዲሶች ሲሆን
የሸሪአ ድንጋጌዎችን ስነ ምግባርን ለምእመናን የተከለከሉ እና የተፈቀዱ ምግባሮችን ያብራራል
በፊቂህ የትምህርት ፕሮግራም ለተማሪዎች ስለ፦
አንድ ሙስሊም ሊያውቀው የሚገባ የ አምልኮ ስርአት
ከ ጡሃራ ጀምሮ እስከ ሀጅ ድረስ
የ ፋይናንሺያል አያይዝና ህግጋቱን በ አጭር መልኩ
የቤተሰብ አስተዳደር እና ቀለል ባለ መልኩ ስለ ህክምና
ስለ መሃላ እና ስለት
ዘመናዊና ጊዜውን ባገናዘበ መልኩ ስለ ምግብ እና መጠጥ
ሁሉም ርእሶች በ ፎቶ ማስረጃ የተደገፈ ትምህርት ሲሆን ከ ከባድ የቋንቋ አጠቃቀም እና ከ አለመግባባቶች የራቀ ነው ፡፡.
በ ሲራ የትምህርት ጊዜ
ሙሉን የነቢዩ ሙሀመድ የህይወት ታሪክ እና ባህሪ በ ቀላል አቀራረብ .
በህይወት ዘመናቸው ስለ ተከናወኑ ክስተቶች
ከ ሰዎች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት
ከ ህይወት ታሪካቸው የ ምናገኘውን ጥቅም እና በመጨረሻም
ኡለማዎች የሰጡትን አስተያየት
በ እስላማዊ ትምህርት(ተርቢያ) ከየትኛውም የትምህርት ካሪኩለም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው የተለያዩ ክፍሎች ያሉት የ አላህ ሀቅ የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀቅ የሰሃባዎች ሀቅ የወላጆች ሀቅ የባል ሀቅ የሚስት ሀቅ……………. በሁለተኛው ክፍል የልብ ስራዎች እነሱም አላህን በፍጹምነት መገዛት ፡በአላህ መመካት የችግር ጊዜ መታገስን ፡ የአላህን ውሳኔንም መውደድ ………… በመጨረሻም እስላማዊ ስነ ምግባር እና የልብ በሽታዎች እና መፍትሄዎቻቸውን