ምስጋና ለአላህ ይሁን ፣ ሰለዋት እና ሰላም ሰዎችን መልካም አስተማሪ በሆኑት በመሐመድ ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይሁን። ከዛም በመቀጠል የሸሪዓ ትምህርት አላህን ለማሰደሰት እና ወደ ከፍተኛ የጀነት ደረጃዎች የሚያደርስ መንገድ ነው ፣ እናም እሱ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻው ዓለም ወደ መልካም ነገር ሁሉ የሚያደርስ ነው ፣ በተጨማሪ የሸሪዐ ትምህርት የግለሰብ እና የህብረተሰብ ደህንነት ጎዳና ነው ፣ እና በእሱ ማህበረሰቦች ክብራቸውን እና መሪነታቸውን ያገኛሉ ፣ እናም ለእውቀት ፈላጊዎች ጥሩ ክብር ነው። አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል- {አላህ በመካከላችሁ ያመኑትን እና እውቀትን የተሰጡትን ከፍ ያደርጋል ፣ አላህም የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ጌታ ነው} [አል- ሙጃደላ 11] እናም እንዲህ ብሏል – {አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ። መላእክቶችና የእውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)።} (ሱረቱል ዒምራን፡18)
የእውቀት ደረጃ አላህ ዘንድ ላቅ ያለ ስፍራ ስላለው አላህ ነቢዩን ሰ.ወ እውቀት እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁት አዘዛቸው ። አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ ( “ጌታዬ እውቀት ጨምርልኝ”በል)። የእውቀትንና ባለቤቶቿን ደረጃ የሚያወሱ በርካታ ቁርአናዊ እና ሀዲሳዊ ማስረጃዎች መጥተዋል ። ነብዩ ሰ ዐወ እንዲህ ብለዋል (እውቀትን ፍለጋ መንገድን የገባ ሰው አላህ ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ ያቀልለታል) ሙስሊም ዘግበውታል
ለዚያም ነው (አፍሪካ አካዳሚ) አረብኛ ተናጋሪዎች ላልሆኑ ለአፍሪካ ማህበረሰቦች የተዘጋጀ በተለያዩ ቋንቋዎቻቸው የሙስሊሞችን የእስልምና ዕውቀት ፍላጎት ለማሟላት እና የእውቀትን ጥያቄ ለማመቻቸት የመጣ በስራ ለተጠመዱ እና ብዙ ትርፍ ሰዓት ላላቸው በኢንተርኔት አማካይነት የመጀመሪያው የኤሌክትሮኒክስ አካዳሚ ይዞ የመጣው ። የአካዳሚው መርሃ ግብር የሚመለከተው በቀደምት ሰዎች ግንዛቤ እና እምነት ላይ በመመርኮዝ ከቁርአን እና ከእውነተኛ ሱና የተገኘውን የሸሪዓ ትምህርት ማስተማር ነው። ሥርዓተ ትምህርቱ ከሸሪዓ ተማሪዎች ጋር ተመጣጣኝ በሆነ ደረጃ የተቋቋመ ሲሆን በቀላልነት እና ሙስሊሙ የሚያስፈልገውን ዕውቀት የሰበሰበ ፣ እና የአመለካከት ልዩነቶችን ከማስፋፋት የራቀ ፣ እና በጥሩ ቴክኒካዊ እና በተለያዩ መንገዶች የተነደፈ ነው። ለተማሪዎች አቀባበልን ለማመቻቸት እና ከጊዜው ጋር ለመራመድ የኮርሶች ዲዛይኖች የእውቀት እድገት እና የዘመናዊ ትምህርት ዘዴዎች የተዘጋጀ ነው።
ይህ የትምህርት ስርጭት ወደ እውቀት መርከብ ለመግባት ውድ የሆነች እድል ናት ። ይህም አንድ ሙስሊም መዳኛውና ህይወቱ እንዲሁም በዱንያም ሆነ በአኺራ ከፍ ያለ ደረጃ ማግኛ የሆነውን እውቀት የህይወቱ መመሪያ እስኪያረግ ድረስ ያዘጋጀነው ፕሮግራም ነው። አላህ እንዲህ ብሏል {አላህ በመካከላችሁ ያመኑትን እና እውቀትን የተሰጡትን ከፍ ያደርጋል ፣ አላህም የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ጌታ ነው} (አልሙጃዲላ 11)
አላህን ለሁላችንም መልካሙን እንዲገጥመን የሸሪዐ እውቀትን በማወቅ እና ተጠቃሚ በመሆን በሱም ላይ ስራችንን ፍፁም ለአላህ እንድናረግ እንዲያግዘን እማፀነዋለው።
የአፍሪካ አካዳሚ የበላይ ጠባቂ