
የመጀመሪያ ዙር የዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት ምረቃአፍሪካ አካዳሚ በአማረኛ ቋንቋ ዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህር የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን በዙል ቅዕዳ ወር መግቢያ 1444ሂ
የሸሪዓ ትምህርት በነፃ የሚያስተምር አፍሪካ ኤሌክትሮኒክ መድረክ
አፍሪካ አካዳሚ በቁርዓን እና በሐዲስ የተደገፉ ትክክለኛ የእስልምና አረዳድ በኢንተርኔት፣ በሶሻል ሚዲያ እና በአፍሪካ ቲቪ አማካይነት ለአፍሪካዊያን ማህበረሰብ ማቅረብን ያለመ ምናባዊ ኤሌክትሮኒክ የትምህርት አካዳሚ ነው።
አፍሪካ አካዳሚ ሰላም ይላቹዋል
የእስላምና ሀይማኖት መሰረታዊ ጉዳዮች እና ማንኛውም ሙስሊም ሊያውቀው የሚገባ ነገሮች የመማር ፍላጎት ላሉት የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በሙሉ፦
ምዝገባው በአካዳሚው ዌብሳይቱ መሰረት አሁን ክፍት ነው።
እንዲሁም ለሁለተኛ ዙር የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል።
ለሁለተኛ ዙር ምዝገባው አሁንም ክፍት ነው። እድሉን ተጠቅመህ ለምዝገባው ፍጠን።
የሁለተኛ ዙር ዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት ፕሮግራም ምዝገባ ተዘግቷል።
ለሶስተኛ ዙር ምዝገባ በአላህ ፍቃድ በቅርቡ ይከፈታል። ምዝገባው መቼ እንደሚጀመር ለማወቅ በዚህ ማህበራዊ መገናኛ ተከታተሉን፦
http://bit.ly/m/Africa-Academy
እንዲሁም በክፍት አጫጭር ኮርስ ላይ በፈለጋችሁ ጊዜ ከዚህ መከታተል ትችላላችሁ፦
https://bit.ly/3LmkeSg
እሱም የተጠናከረ እውቀታዊ የሸሪዓ ፕሮግራም ሲሆን ጊዜ ገደቡ አንድ አመት ብቻ ነው። ስርዓተ-ትምህርቱ በአመት አንዴ ምዝገባው የሚከፍት ሲሆን እሱም ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት በበቂ ጊዜ በሶሻል ሚዲያ እና በአፍሪካ ቲቪ ላይ ይፋ ይደረጋል። የዲፕሎማው ፕሮግራም በውስጡ ሁለት ሴሚስተር የያዘ ሲሆን ተማሪዎቹ በነዚህ ሁለት ሴሚስተሮች በየአንዳንዱ ሴሚስተር ስድስት የትምህርት አይነቶችን ይማራል። ተማሪው የሁለቱም ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ካለፈ በኋላ ከአካዳሚው የማጠናቀቂያ ምስክር ወረቀት ይወስዳል።
እሱም አጫጭር የሸሪዓ ኮርሶች ጥርቅም ሲሆን አንድ ሙስሊም ሊያውቀው ከሚገባ የእስልምና ምዕራፎች ውስጥ አንድና ከዛ በላይ ርዕሶችን የሚዳስስ ነው። ተማሪው በሚፈልግበት ጊዜ፣ በሚመቸው ሰዓት እና በሚችለው መጠን ይማር ዘንድ ምዝገባው ምንጊዜም ክፍት ነው። ኮርሱን ከአጠናቀቀ እና ፈተናውን ከለፉ በኋላ ተማሪው ያጠናቀቀውን ኮርስ በተመለከተ የማጠናቀቂያ ምስክር ወረቀት ይወሰዳል።
16085
660
9176